- በየትኛውም ጉዳይ በተለይም በዒባዳና ፃድቃንን በማላቅ ረገድ ወሰን ማለፍና ያላቅም መንጠራራት መከልከሉ፤ ከእንዲህ አይነቱ ነገር መራቁ በየትኛውም ጉዳይ ላይ እንደሚበረታታ፤
- በአምልኮም ይሁን በሌላው ጉዳይ ተስተካክሎ የተሟላውን መፈለግ እንደሚገባ፤ ይህም የሚሆነው ሸሪዓውን በመከተል መሆኑ፤
- አሳሳቢ ጉዳይ ላይ ጠንከር ማድረግ እንደሚገባ፤ ምክንያቱም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ይህንኑ እንኳ ሲናገሩ ሶስት ጊዜ ደጋግመው ነውና የተናገሩት።
- የእስልምና ገራገርነትና ቀላልነትን እንረዳለን።