- የነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ግልፅ ተአምርን እንመለከታለን። ይህ መገለጫ ለአላህ ምስጋና ይግባውና ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ከመኖር አልተወገደምና። ሐዲሡ ውስጥ የተጠቀሰው የአላህ ትእዛዝ እስኪመጣ ድረስም ከመኖር አይወገድም።
- በሐቅ ላይ የመፅናትና በርሱም የመስራት ትሩፋትን በዚህ ላይም መነሳሳቱን እንረዳለን።
- የዲን የበላይነት ሁለት አይነት ነው: ወይ የማስረጃና እውነታን የማብራራት የበላይነት ነው። ወይም የሀይልና የመሳሪያ የበላይነት ነው። የማስረጃና ማብራራት የበላይነት ዘውትር ያለ ጉዳይ ነው። ምክንያቱም የእስልምና ማስረጃ ቁርአን ነውና። ቁርአን ደግሞ ከርሱ ውጪ ባሉት ላይ ሁሌ የበላይና አሸናፊ ነው። ነገር ግን ሁለተኛው የበላይነት አይነት ማለትም የሀይልና የመሳሪያ የበላይነት በኢማንና በምድር እንደሚኖር መመቻቸት መጠን የሚወሰን ነው።