- የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መልክተኝነት ዓለምን በሙሉ የሚጠቀልል መሆኑን፣ እሳቸውን መከተልም ግዴታ መሆኑን፣ በሳቸው ድንጋጌ ሁሉም ድንጋጌዎች መሻራቸውንም እንረዳለን።
- በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የካደ ሰው ከሳቸው ውጪ ባሉ ነቢያቶች የአላህ ሶላትና ሰላም በነርሱ ላይ ይስፈንና እንደሚያምን መሞገቱ አይጠቅመውም።
- ስለ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያልሰማና የኢስላም ጥሪ ያልደረሰው ሰው ተቀባይነት ያለው ምክንያት ስላለው የርሱ ጉዳይ በመጨረሻው አለም አላህ ዘንድ ነው።
- ነፍስ ልትወጣ ጉሮሮ ላይ እስካልደረሰች ድረስ ከባድ በሽታ ላይ ሆኖ እንኳ ቢሆን የሰለመ እስልምናው ከመሞቱ በፊት እስከሆነ ድረስ በኢስላም የሚገኘው ጥቅም የተረጋገጠ ነው።
- የከሀዲያንን ሃይማኖት ትክክለኛ እምነት አድርጎ ማሰብ ክህደት ነው። (ከነርሱም ውስጥ አይሁድና ክርስትና ይገኛሉ።)
- አይሁድና ክርስትናን በሐዲሡ ውስጥ መጠቀሳቸው ከነርሱ ውጪ ያሉትን አፅንኦት ለመስጠት ነው። ይህም አይሁድና ክርስቲያኖች መጽሐፍ እያላቸውም የነርሱ ጉዳይ እንዲህ ከሆነ ከነርሱ ውጪ መጽሐፍ የሌላቸው ደሞ በበለጠ መልኩ መንገድ የሐዲሡ መልእክት ውስጥ ይገባሉ። ስለሆነም ሁሉም በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እምነትና መመርያ ውስጥ መግባት ግዴታቸው ነው።