- በሐዲስ እንደተረጋገጠው የጀናዛ ሶላት ካልሆነ በቀር በመቃብር ስፍራ ወይም በመቃብሮች መካከል ወይም ወደ መቃብር ዙሮ መስገድ ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
- ወደ መቃብር መስገድ የተከለከለው የሺርክን መዳረሻዎች ለመዝጋት ነው።
- ኢስላም በመቃብር ወሰን ማለፍንም መቃብር ማዋረድንም ከልክሏል። ወሰን ማለፍም ማሳነስም የለምና።
- ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "የሙትን አጥንት መስበር በህይወት እንደመስበር ነው።" ስላሉ የሙስሊም ክብር ከሞተ በኋላም ዘላቂ ነው።