- ስራን ለአላህ ማጥራት ግዴታነቱንና ከይዩልኝም መጠንቀቅ እንዳለብን እንረዳለን።
- ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለኡመታቸው ያላቸውን ከባድ እዝነት፣ በመመራታቸው ላይ ያላቸውን ጉጉትና ለነርሱ ያላቸውን ተቆርቋሪነት እንረዳለን።
- ሶሐቦች የደጋጎች አለቃ ከመሆናቸውም ጋር ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶሐቦችን ሲያናግሩ በዚህ ልክ የሚፈሩላቸው ከሆነ ከነርሱ በኋላ ባሉ ሰዎች ላይ ያላቸው ፍርሀት እጅግ የከበደ መሆኑን እንረዳለን።