- ከአደን ውሻና ከጥበቃ ውሻ በቀር ውሻ መያዝና መጎዳኘት መከልከሉን እንረዳለን።
- ከመጎዳኘት የሚቆጠቡት መላእክቶች የእዝነት መላእክት ናቸው። የሰውን ስራ የሚቆጣጠሩት መላእክት ግን ባሮችን ቤታቸውም ውስጥ ሆነው ጉዞም ላይ አይለዩዋቸውም።
- ቃጭል መከልከሉን እንረዳለን። ምክንያቱም እርሱ ከሰይጣን መዝሙሮች መካከል አንዱ ነውና። ቃጭል በውስጡ የክርስቲያኖች ደወል ጋር መመሳሰልን ያቀፈ ነው።
- አንድ ሙስሊም መላእክትን የሚያርቅ ከሆነ ነገር ሁሉ በመራቅ ላይ ሊጓጓ እንደሚገባ እንረዳለን።