- "አላህና አንተ ሽታቹሀል።" ማለትና ይህን የመሳሰሉ ቃላቶችን በ "እና" አጣምሮ አሏህ ጋር መጠቀም የቃላትና የንግግር ሺርክ ስለሆነ ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
- "አላህ ሽቶታል ከዚያም አንተ ሽተኸዋል" የሚለው ንግግርና ይህን የመሳሰሉ "ከዚያም" በሚለው መስተፃምር አሏህ ጋር መጠቀም የተከለከለው ነገር ስለሚወገድ ይፈቀዳል።
- ለአላህ መሻት እንደምናፀድቅለት፣ ለባሪያም መሻት እንደምናፀድቅለት እና የባሪያ መሻት የአላህን መሻት ተከትሎ የሚመጣ መሆኑን እንረዳለን።
- በቃል ደረጃ እንኳ ቢሆን በአላህ መሻት ላይ ፍጡራንን ማጋራት መከልከሉን እንረዳለን።
- ተናጋሪው የባሪያ መሻት እንደ አላህ መሻት ነው፤ ከአላህ መሻት ጋር በአካታችነትም ይሁን በስፋት እኩል ነው ብሎ ካመነ ወይም ባሪያ ራሱን የቻለ (አላህ ባይሻለትም) የመሻት አቅም አለው ብሎ ካመነ ትልቁ ሺርክ ይሆናል። ከአላህ በታች የሆነ መሻት ነው ያለው ብሎ ካመነ ግን ትንሹ ሺርክ ይሆናል።