- አላህን ማመፅ ላይ እስካልሆነ ድረስ መሪዎችን መታዘዝ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
- እዚህ ሐዲሥ ውስጥ ከመሪ ትእዛዝ የወጣና ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ያፈነገጠ ላይ ከባድ ማስጠንቀቂያ አለ። በዚህ ሁኔታ ላይ ሆኖ ቢሞት የድንቁርናው ዘመን ሰዎች መንገድ ላይ ሆኖ ሙቷል።
- ሐዲሡ ውስጥ ለወገንተኝነት ብሎ መዋጋት ክልክል መሆኑ ተገልጿል።
- ቃል ኪዳንን መሙላት ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
- መሪን በመታዘዝና አንድነትን በመጠበቅ ደህንነት፣ መረጋጋት፣ የሁኔታዎች መስተካከልና የመሳሰሉት ብዙ በጎ ነገሮች ይገኛሉ።
- ከድንቁርና ዘመን ባለቤቶች ሁኔታ ጋር መመሳሰል መከልከሉን እንረዳለን።
- የሙስሊሙን ህብረት አጥብቆ መያዝ መታዘዙን እንረዳለን።