- ከአላህ ውጪ መማል ክልክል መሆኑን እንረዳለን። ከዚህም መካከል በአደራ መማል አንዱ ነው። ይህም ከትንሹ ሺርክ መካከል ነው።
- አማና የምትለዋ ቃል ትእዛዝን፣ አምልኮን፣ አደራን፣ ገንዘብንና ደህንነትን የሚጠቀልል የወል ስም ነው።
- መሃላ በአላህ ወይም ከስሞቹ መካከል በአንድ ስሙ ወይም ከባህሪያቶቹ መካከል በአንድ ባህሪው ካልሆነ በቀር አይታሰርም።
- ኸጧቢይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ክልከላ የመጣው እርሳቸው በአላህና በባህሪያቱ እንዲምል ስላዘዙ ይመስላል። አደራ ደሞ ከአላህ ባህሪያቶች መካከል ሳይሆን ከትእዛዞቹ መካከል አንድ ትእዛዙ፣ ከግዴታዎቹ መካከል አንዱ ግዴታው ነው። ከዚህ የተከለከሉትም በርሷ መካከልና በአላህ ስምና ባህሪያት መካከል እኩል ማድረግ ስለሚሆን ነው።"