- ከአላህ በቀር መልካምን የሚያመጣና ከአላህ በቀርም መጥፎን የሚከላከል ስለሌለ በአላህ ላይ መመካት እንደሚገባ እንረዳለን።
- የገድ እምነት መከልከሉን እንረዳለን። እርሱም ሰው ገድ የሚልበትና ከስራ የሚያቅበው ነገር ነው።
- "አልፈእል" ከተከለከለው የገድ እምነት መካከል አይደለም። ይልቁንም ያ በአላህ ላይ መልካም እሳቤ ማሳደር ነው።
- ሁሉም ነገር በብቸኛውና አጋር በሌለው በአላህ ውሳኔ ነው የሚከሰተው።