- ከዝናብ መውረድ በኋላ፦ በአላህ ችሮታና እዝነት ዘነበልን ማለት እንደሚወደድ።
- የዝናብ መውረድና ሌሎችን ፀጋዎች መፍጠሩንም ሆነ ማስገኘቱን ወደ ከዋክብት ያስጠጋ ትልቁን ክህደት የካደ ሲሆን ወደ ከዋክብት በሰበብ ደረጃ ካስጠጋ ደግሞ ትንሹን ክህደት የካደ ይሆናል። ምክንያቱም ሸሪዐዊም ሆነ ህዋሳዊ ሰበብ አይደለምና።
- አንድ ፀጋ በተካደ ጊዜ የክህደት ምክንያት ሲሆን፤ ተገቢ ምስጋና ከቀረበበት ደግሞ የኢማን ምክንያት ይሆናል።
- የሽርክን መዳረሻ ለመዝጋት ሲባል ወቅቱን ለመግለፅ ተፈልጎበት ቢሆን እንኳን "በእንዲህ ኮኮብ እንቅስቃሴ ምክንያት ዘነበልን" ማለት መከልከሉ፤
- ፀጋን በማምጣትና መአትን በመከላከል ረገድ ቀልብን በአላህ ላይ ማንጠልጠል ግዴታ መሆኑን ተረድተናል።