- የጥንቆላ ክልክልነትን ፣ ወደጠንቋዮች መሄድና ስለሩቅ ሚስጥር መጠየቅም ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
- ሰው ለወንጀሉ መቀጣጫ ይሆን ዘንድ የመልካም ስራውን ምንዳ ሊከለከል እንደሚችል እንረዳለን።
- አስትሮኖሚ (ዞዲያክ/ኮከብ ቆጠራ) በመባል የሚጠራው እውቀትና ወደርሱ መመልከት ፣ መዳፍና ሲኒን ለማወቅ ያህል ብቻ እንኳ ቢሆን ማንበብ እዚህ ሐዲሥ ውስጥ ይካተታል። ምክንያቱም ይህ ሁሉ ከጥንቆላና የሩቅ ምስጢር እውቀትን በመሞገት ውስጥ የሚመደብ ነውና።
- ሩቅ ሚስጥር አዋቂ ነኝ ባይ ጋር የሄደ ሰው ምንዳው ይህ ከሆነ ራሱ ሩቅ ሚስጥር አዋቂ ነኝ ባዩ ምንዳው ምን ይሆን?
- የአርባ ቀን ሶላቱ ስለምታብቃቃው ቀዳ የማውጣት ግዴታ አይኖርበትም። ነገር ግን በርሷ ምንም ምንዳ አያገኝም።