- የነቢያቶችንና ደጋጎችን መቃብር ለአላህ የሚሰገድበት መስገጃ አድርጎ መያዝ ወደ ሺርክ የሚያዳርስ ስለሆነ መከልከሉን እንረዳለን።
- የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በተውሒድ ላይ ያላቸው ትኩረትና ጥንቃቄ የበረታ መሆኑንና መቃብርን ማላቅም ወደ ሺርክ ስለሚያዳርስ መስጋታቸውን እንረዳለን።
- አይሁዶችንና ክርስቲያኖችን መርገም እንዲሁም ቀብር ላይ በመገንባትና መቃብርን መስገጃ አድርጎ በመያዝ የነርሱን ድርጊት አምሳያ የሰራን ሰውም መርገም እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
- በመቃብር ላይ መገንባት የአይሁዶችና ክርስቲያኖች ሱና መሆኑንና ሐዲሡ ከነርሱ ጋር መመሳሰልንም ይከለክላል።
- መስገጃ ባይገነባበት እንኳ እርሱ ዘንድ መስገድና ወደርሱ ዙሮ መስገድ መቃብርን መስገጃ አድርጎ መያዝ ውስጥ ይካተታል።