- ቁርኣን እንደሚከበረውና ከሱ ድንጋጌዎች እንደሚወሰደው ሁሉ ሱናንም ማላቅ እንደሚገባ።
- መልክተኛውን መታዘዝ አላህን መታዘዝ ነው፤ እሳቸውንም አለመታዘዝ አላህን አለመታዘዝ ነው።
- የሐዲሥ ማስረጃነት የፀና መሆኑና ሐዲሥን የማይቀበል ወይም የሚያወግዝ ሰው ላይ በቂ ምላሽ መሰጠቱ።
- ከሐዲሥ በማፈንገጥ በቁርኣን ብቻ መብቃቃትን የሞገተ ሰው፥ በሁለቱም ላይ ያፈነገጠና ቁርኣንን እከተላለሁ የሚለው ሙግቱም ቅጥፈት እንደሆነ ያስረዳል።
- የነቢዩን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ነቢይነት ከሚጠቁሙ ነገሮች መካከል ለወደፊት ይከሰታል ብለው የተናገሩት ነገር እንደተናገሩት መከሰቱ ነው።