- መልክተኛውን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መታዘዝ አላህን ከመታዘዝ ይመደባል። እሳቸውን ማመፅም አላህን ከማመፅ ይመደባል።
- ነቢዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መታዘዝ ጀነት መግባትን ስታስፈርድ እሳቸውን ማመፅ ደግሞ እሳት መግባትን የምታስፈርድ መሆኗ።
- ከዚህ ኡማህ አላህና መልክተኛውን ያመፁ ሲቀሩ ነቢዩን ታዛዥ ለሆኑ ብስራት ነው፤ ሁሉም ጀነት ይገባሉና።
- ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በኡመታቸው ላይ ያላቸውን እዝነትና እንዲመሩ ያላቸውን ጥልቅ ጉጉት እንረዳለን።