- መልካም ስራዎች በደረጃ እንደሚበላለጡት ሁሉ ወንጀሎችም በከባድነታቸው ይበላለጣሉ።
- እጅግ ትልቁ ወንጀል በአላህ ማጋራት ነው። ቀጥሎ ከአንተ ጋር መብላቱን በመፍራት ልጅን መግደል ነው። ቀጥሎም በጎረቤት ሚስት ላይ ዝሙት መፈፀም ነው።
- ሲሳይ በአላህ እጅ ነው። ጥራት የተገባው አላህ በፍጡራን ሲሳይ ላይ ኃላፊነቱን ወስዷል።
- የጎረቤት ሐቅ ታላቅ መሆኑንና ጎረቤትን የማወክ ወንጀልነቱ ሌላን አካል ከማወክ የበለጠ እጅግ የከፋ ወንጀል መሆኑን እንረዳለን።
- ፈጣሪ ብቸኛው ለአምልኮ የተገባና አጋር የሌለው ነው።