- ወደ ሽርክ የሚያደርስ በመሆኑ በማላቅ እና በማወደስ ረገድ ሸሪዓ የደነገገውን ገደብ ከማለፍ መጠንቀቅ እንደሚገባ፤
- ይህ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ያስጠነቀቁት ነገር በእውነቱ በዚህ ኡማ ተከስቷል። ይህም የተወሰኑት ነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ላይ፣ ከፊሎች የነቢዩ ﷺየአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ቤተሰቦች ላይ፣ ሌሎች ደግሞ ወልዮች ላይ ይህ ያስጠነቀቁትን ነገር በመፈፀም ሽርክ ላይ ወድቀዋል።
- የአላህ መልእክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የአሏህ ባሪያው ናቸው እንጂ ከአምላክ መለያዎች መካከል የትኛውም እንደማይገባቸው ለመጠቆም ራሳቸው የአላህ ባሪያ መሆናቸውን ገለፁ።
- ረሱል የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ከአሏህ የተላኩ መልዕክተኛው በመሆናቸው ሊያምኗቸውና ሊከተሏቸው እንደሚገባ ለመጠቆም ራሳቸውን የአሏህ መልዕክተኛ መሆናቸውንም ገለፁ።