- ቤቶች አሏህን ከማምለክ መገለላቸው የተከለከለ መሆኑ፤
- የነቢዩን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ቀብር ለመዘየር አስቦ ጉዞ መውጣት መከልከሉን፤ ምክንያቱም ሶለዋት በሳቸው ላይ እንድናወርድና እንደሚደርሳቸውም ነግረውናልና። በአምልኮ መንፈስ ጉዞ የሚወጣው ወደ መስጂዱ ለመሄድና እዛው ለመስገድ ከሆነ ብቻ ነው።
- በተለየ መልኩና በተለየ ጊዜ የርሳቸውን ቀብር ደጋግሞ መጎብኘትን ልምድ አድርጎ መያዝ መከልከሉ፤ የሌላን ቀብርም ቢሆን እንደዚሁ የተከለከለ ነው።
- የላቀው አሏህ ከየትኛውም ቦታና በማንኛውም ጊዜ በሳቸው ላይ ሶለዋት ማውረድን መደንገጉ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አምላካቸው ዘንድ ያላቸውን ከፍተኛ ደረጃ ያሳያል።
- መቃብር ዘንድ መስገድ መከልከሉ ሶሓቦች ዘንድ የፀና ጉዳይ በመሆኑ ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ባልደረቦቻቸው ቤቶቻቸውንም እንደመቃብሩ የማይሰገድበት እንዳያደርጉ ከለከሏቸው።