- አስፈላጊና አንገብጋቢ በሆነ ነገር ላይ መጠመድ ተገቢ ነው። ለጊዜው አስፈላጊ ያልሆነን ነገር መተውና ያልተከሰተን ነገር በመጠየቅ ከመጠመድ መታቀብም ተገቢ ነው።
- ምናልባትም ጉዳዮችን ወደ መወሳሰብ የሚያደርስና ልዩነት እንዲበዛ መንስኤ የሚሆን የውዥንብርን በር የሚከፍት ጥያቄ መጠየቅ ክልክል ነው።
- ሁሉንም ክልከላዎች በመተው መታዘዙ። ምክንያቱም መተዉ ምንም ስለማይከብድ ነው። ስለዚህም ነው ክልከላው አጠቃላይ የሆነው።
- ትእዛዛትን መፈፀም ከአቅምና ችሎታ ጋር የተቆራኘ መሆኑን እንረዳለን። ይህም አንዳንዴ ትእዛዝን መፈፀም ሊከብድ ወይም አለመቻል ሊገጥም ይሆናል። ስለዚህም ትእዛዝን መፈፀም የታዘዘው ከአቅም ጋር ተቆራኝቶ ሆነ።
- ጥያቄን ማብዛት መከልከሉን እንረዳለን። ዑለማዎች መጠየቅን ለሁለት ከፍለውታል: አንደኛው: የሚያስፈልገውን ሃይማኖታዊ ጉዳይ በመማር መልኩ መጠየቅ ነው። በዚህ አላማ መጠየቅ ታዟል። የሶሐቦችም ጥያቄ በዚህ መልኩ ነበር። ሁለተኛው: ጥያቄን በመጨነቅና በግትርነት መልኩ መጠየቅ ሲሆን ይህኛው ግን የተከለከለው የመጠየቅ አይነት ነው።
- ይህ ኡማ ከዚህ በፊት የነበሩት ህዝቦች ነቢያቸውን እንደተቃረኑት ነቢያቸውን ከመቃረን መከልከላቸውን እንረዳለን።
- የማያስፈልግ ጥያቄ ማብዛትና ነቢያቶችን መቃረን የጥፋት ሰበብ ነው። በተለይ መልሱ የማይደረስበትን ጥያቄ መጠየቅ ለምሳሌ: ከአላህ በቀር ማንም የማያውቃቸውን የሩቅ እውቀት፣ የትንሳኤ ቀንን ሁኔታዎች መጠየቅ ይገኙበታል።
- ከባባድ ርዕሶችን ከመጠየቅ መከልከሉ። አውዛዒ እንዲህ ብለዋል: "አላህ የእውቀትን በረከት ባሪያውን ሊነፍገው የፈለገ ጊዜ ምላሱ ላይ ጥያቄ ማብዛትን ይጥልበታል። እንደዚ አይነት ሰዎችን ትንሽ እውቀት ያላቸው ሆነው አግኝቻቸዋለሁ።" ኢብኑ ወህብ እንዲህ ብለዋል: ማሊክ እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "እውቀትን መከራከር ከሰውዬው ቀልብ ውስጥ የእውቀትን ብርሀን ያስወግዳል።"