- የአላህን ሸሪዓ ማስተላለፍ እንደሚበረታታና ማንኛውም ሰው የሸመደደውና የተረዳውን ትንሽም ቢሆን ማድረስ እንዳለበት፤
- አሏህን በትክክል ለማምለክና መልዕክቱንም ለማድረስ እንዲያስችል ሸሪዓዊ እውቀትን መፈለግ ግዴታ መሆኑን፤
- ይህ ከባድ ዛቻ ከሚመለከታቸው ሰዎች ላለመሆን ሲባል የትኛውንም ሐዲሥ ከማስተላለፋችንና ከማሰራጨታችን በፊት በትክክል ከሳቸው መሆኑን ማረጋገጥ ግዴታ እንደሆነ፤
- ውሸት ላይ ላለመውደቅ ሲባል በተለይም በአሏህ ሸሪዓ ላይ በንግግራችን እውነተኞችና የምናወራውም የተሟላ መረጃው ያለንን ጉዳይ መሆኑ እንደሚበረታታ እንረዳለን።