- መልክተኛውን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መውደድና ከሁሉም ፍጡራን ውዴታ ማስቀደም ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
- የአላህን መልክተኛ ሱና መርዳትና በዚህ መንገድ ላይም ገንዘብና ነፍስን መለገስ ከተሟላ ውዴታ ምልክቶች መካከል አንዱ ነው።
- መልክተኛውን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መውደድ ባዘዙት ነገር መታዘዝን ፣ በተናገሩት ማመንን፣ ከከለከሉትና ካስጠነቀቁት ነገሮች መከልከልን፣ እሳቸውን መከተልንና ቢድዓን መተው ያስፈርዳል።
- ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከጥመት መንገድ (ወደ ቀናው) ለመመራታችን ፣ ከእሳት ለመዳናችን፣ ጀነትን ለመጎናፀፋችን ምክንያት ስለሆኑ የነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሀቅ ከሁሉም ሰዎች ሀቅ የበለጠና የገዘፈ ነው።