- ወደ ሺርክ የሚያደርስን መንገድ ለመዝጋት ሲባል በመቃብሮች ላይ መስጊዶች መገንባት ወይም እርሷ ዘንድ መስገድ ወይም መስጊድ ውስጥ ሟቾችን መቅበር ክልክል ነው።
- መቃብሮች ላይ መስጂዶችን መገንባትና ስእሎችን መስጅድ ውስጥ መስቀል የአይሁድና ክርስቲያኖች ስራ መሆኑንና ይህንን የፈፀመም ከነርሱ ጋር መመሳሰሉን እንረዳለን።
- ነፍስ ያላቸውን ነገሮች ስእል መያዝ ክልክል መሆኑ።
- ቀብር ላይ መስጂድ የገነባ፣ መስጂድ ውስጥም (ነፍስ ያላቸው) ስእሎችን የሳለ ሰው ከክፉዎቹ የአላህ ፍጡሮች መካከል ነው።
- ሸሪዓ ወደ ሺርክ የሚያደርሱ መንገዶችን ባጠቃላይ በመዝጋቱ ሸሪዓ የተውሒድን ዳር ድንበር ሙሉ ለሙሉ መጠበቁን እንረዳለን።
- በደጋጎች ላይ ወሰን ማለፍ ሺርክ ላይ ለመውደቅ ምክንያት ስለሆነ ክልክል ነው።