ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ትክክለኛውን አካሄድ...
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሶሐቦች እንዲሰሩ፤ ወሰን ሳያልፉና ሳያጓድሉ በቻሉት ልክ አላህንም እንዲፈሩ፤ ስራቸው ተቀባይነት አግኝቶ በነርሱ ላይ የአላህ እዝነት እንዲወርድ ሰበብ እንዲሆ...
ከኢብኑ ዑመር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "(ጎረቤቴን) ያስወርሰዋል ብዬ እስከማስብ ድረስ ጂብሪል በጎረቤት (ሐቅ ዙሪያ) እኔን ከማዘዝ አል...
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጂብሪል ለጎረቤታቸው ትኩረት እንዲቸሩ፣ ሐቁን እንዲጠብቁ፣ እንዳያውኩት፣ ለርሱ በጎ እንዲውሉ፣ በሚያደርስባቸው ጉዳት እንዲታገሱ ከማዘዝና ከመደጋገም እንዳልተወገደ ተናገሩ። ይህም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለ...
ከአቡ ደርዳእ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "ከወንድሙ ክብር የተከላከለ ሰው በትንሳኤ ቀን አላህ እሳትን ከፊቱ ይከላከልለታል።"
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሙስሊም ወንድሙ በራቀ ወቅት እንዳይወገዝ ወይም በርሱ ላይ መጥፎ እንዳይደርስበት በመከልከል ከሙስሊም ወንድሙ ክብር ለተከላከለ ሰው አላህ የትንሳኤ ቀን ቅጣትን ከሱ እንደሚከላከልለት ተና...
ከአነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አንዳችሁ ለነፍሱ የሚወደውን ነገር ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ አላመነም።"
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለነፍሱ የሚወደውን አምልኮዎችና ሃይማኖታዊም ይሁን ዱንያዊ መልካም ነገሮችን ለወንድሙ እስከሚወድ ድረስ፤ ለነፍሱ የሚጠላውንም ለርሱም እስኪጠላ ድረስ ለአንድ ሙስሊም የተሟላ ኢማን እ...
የነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ባለቤት ከሆነችው ከእናታችን ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "በአንድ ነገር ውስጥ ገራገርነት (ልስላሴ) አይኖርም ያስዋበው ቢሆን...
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በንግግርም ይሁን በተግባር ገራገርነት፣ ለስላሳነትና እርጋታ ነገሮች ላይ ውበት፣ ምሉዕነትና ማማር የሚጨምር እንዲሁም ይህንኑ ባህሪ የተላበሰ ሰውም ጉዳዩን ለማሳካት የተገባ እንደሆነ ገለፁ። ገራገር (ለ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ትክክለኛውን አካሄድ ተከተሉ፤ በተቻለ መጠን ወደ እሱ ቅርብ ለመሆን ሞክሩ ከናንተ መካከል አንድም ሰው በስራው እንደማይድንም እወቁ!" ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እርሶም ቢሆኑ በስራዎት አይድኑምን?" አሉ። እርሳቸውም "አላህ ከርሱ በሆነ እዝነትና ችሮታ ካልሸፈነኝ በቀር እኔም ብሆን በስራዬ አልድንም።" አሉ።»

ከኢብኑ ዑመር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "(ጎረቤቴን) ያስወርሰዋል ብዬ እስከማስብ ድረስ ጂብሪል በጎረቤት (ሐቅ ዙሪያ) እኔን ከማዘዝ አልተወገደም።"

ከአቡ ደርዳእ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "ከወንድሙ ክብር የተከላከለ ሰው በትንሳኤ ቀን አላህ እሳትን ከፊቱ ይከላከልለታል።"

ከአነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አንዳችሁ ለነፍሱ የሚወደውን ነገር ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ አላመነም።"

የነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ባለቤት ከሆነችው ከእናታችን ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "በአንድ ነገር ውስጥ ገራገርነት (ልስላሴ) አይኖርም ያስዋበው ቢሆን እንጂ ፤ ከአንድ ነገር ውስጥ ደግሞ አይነሳም አስቀያሚ የሚያደርገው ቢሆን እንጂ።"

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "የእስልምና ሃይማኖት ገር ነው። አንድም ሰው የእስልምናን ሃይማኖት ከመጠን በላይ አያጠብቅም (ሃይማኖቱ) የሚያሸንፈው ቢሆን እንጂ፤ ሚዛናዊ ሁኑ! አቀራርቡ! አብሽሩ! በማለዳ አምልኮ፣ በቀትር አምልኮና በተወሰነ የሌሊት አምልኮ ታገዙ!"

ከአነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "አግራሩ አታክብዱ! አበስሩ አታሽሹ!"

ከአነስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ዑመር ዘንድ ነበርንና እንዲህ አሉ: 'ከአቅም በላይ ከመጣጣር ተከልክለናል።'"

ከኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "አንዳችሁ የበላ ጊዜ በቀኙ ይብላ። የጠጣም ጊዜ በቀኙ ይጠጣ። ሰይጣን የሚበላውም በግራው፤ የሚጠጣውም በግራው ነውና።"

ከዑመር ቢን አቢ ሰለማህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "በአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጎጆ ውስጥ የምኖር ህፃን ልጅ ነበርኩ። በማዕዱ ላይም እጄ ትሽከረከር ነበር። የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለኔ እንዲህ አሉኝ ' አንተ ልጅ ሆይ! ቢስሚላህ በል! በቀኝህ ብላ፣ ፊትህ ካለውም ብላ!' ከዚያን ጊዜ በኋላ ከዚህ የአበላል ስርአት አልተወገድኩም።"

ከአነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብሏል: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ 'አላህ ባሪያው ምግብን በልቶ እንዲያመሰግነው ወይም መጠጥን ጠጥቶ እንዲያመሰግነው ይወዳል።'"

ከሰለማ ቢን አክወዕ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው፦ "አንድ ሰውዬ የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ በግራ እጁ በላ። እርሳቸውም 'በቀኝህ ብላ።' አሉት። እርሱም 'አልችልም!' አላቸው። እርሳቸውም 'አያስችልህ!' አሉት። ኩራት እንጂ ሌላ አልከለከለውም። ሰለማ እንዲህ አለ '(ከዛ በኃላ) እጁን ወደ አፉ ማንሳት አልቻለም።' "