- የጎረቤት ሐቅ ክብደትንና ይህንን መጠባበቅ ግዴታ እንደሆነ ፤
- የጎረቤት ሐቅ በአደራ መልክ መጠንከሩ ጎረቤትን ማክበርን፣ መውደድን፣ ለርሱ በጎ መዋልን፣ ከርሱ ጉዳትን መከላከልን፣ ሲታመም መጠየቅን፣ በደስታ ወቅት ማስደሰትን፣ በመከራ ወቅት ማፅናናትን ያስፈርዳል ፤
- የጎረቤት ደጃፍ በቀረበ ልክ ሐቁም የጠነከረ ይሆናል።
- ሸሪዓ ለጎረቤት በጎ መዋልና ከነሱ ላይ ጉዳትን መከላከልን የመሰለ ለማህበረሰቡ ጥቅም ያላቸው ድንጋጌዎችን ይዞ በመምጣቱ ረገድ የተሟላ መሆኑን እንረዳለን።