- የእስልምና ሸሪዓ ገርነትና ቀላልነትን፤ በቸልተኝነትና ወሰን በማለፍ መካከል ሚዛናዊ መሆኑን እንረዳለን።
- አንድ ባሪያ በቻለው ልክ ሳይዘናጋ ወይም ከወሰን በላይ ሳያጠብቅ የታዘዘውን መፈፀም አለበት።
- አንድ ባሪያ አምልኮ ሲፈፅም የንቃት ወቅቱን መምረጥ እንደሚገባው እንረዳለን። በተለይ እነዚህ ሶስት ወቅቶች አንድ ባሪያ ሰውነቱ ለአምልኮ ነቃ የሚልበት ወቅቶች ናቸው።
- ኢብኑ ሐጀር አልዐስቀላኒ እንዲህ ብለዋል: «ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ወደሆነ ቦታ መሄድ ያለመን አንድ መንገደኛን የሚያናግሩ ነው የመሰሉት። እነዚህ ሶስት ወቅቶች ለመንገደኛ ምርጥ ወቅቶች ናቸው። ስለዚህ እኛም የንቃት ወቅቶችን እንድንሰራባቸው አስገነዘቡ። ምክንያቱም አንድ ተጓዥ ሌሊቱንም ቀኑንም በሙሉ ከተጓዘ ይደክምና ጉዞውን ያቋርጣል። በነዚህ የሚያነቁ በሆኑ ወቅቶች መጓዝ ላይ ከበረታ ግን ያለምንም ችግር በጉዞው ላይ ለመዘውተር ይመቸዋል።»
- ኢብኑ ሐጀር እንዲህም ብለዋል: «በዚህ ሐዲሥ ውስጥ ሸሪዓዊ ማግራሪያዎችን መያዝ እንደሚገባ ተጠቁሟል። በተግራራ ቦታ ላይ ከባዱን ግዴታ ነገር መስራት ማካበድ ነው። ለምሳሌ ውሃ መጠቀም ያልቻለና ውሃን መጠቀሙ ጉዳት የሚያደርስበት በሆነ ወቅት ተየሙምን ትቶ ውሃ ቢጠቀም ማለት ነው።»
- ኢብኑ ሙኒር እንዲህ ብለዋል: «በዚህ ሐዲሥ ውስጥ ከነቢያት ምልክቶች መካከል አንዱ ተገልጿል። ይህም እኛም ሆንን ከኛ በፊት የነበሩት በእስልምና ውስጥ ወሰን የሚያልፍ ሰው የሆነ ቦታ ላይ ሲያቋርጥ ማየታችን ነው። በዚህ ሐዲሥ የተሟላን አምልኮ ለመስራት መፈለግን መተው አይደለም የተወገዘው። ይህማ የተወደሰ ጉዳይ ነው። ይልቁንም ወደ መሰላቸት የሚያመራ ወሰን ማለፍ ወይም የተሻለን ለመተው ወይም የግዴታ ነገር ወቅቱ እንዲያልፍ የሚያደርግ በሆነ መልኩ ትርፍ ስራዎች ላይ ወሰን ማለፍ ነው የተከለከለው። ለምሳሌ ያህል ሌሊቱን ሙሉ እየሰገድ አድሮ ሱብሒን በህብረት ሳይሰግድ ወይም ፀሀይ እሰወክትወጣበትና የግዴታው ወቅት እስኪያልፍ ድረስ የሚቆይ ሰው ይጠቀሳል።»