- ከመብላትና መጠጣት ስርአቶች መካከል መጀመሪያ ቢስሚላህ ማለት አንዱ ነው።
- ህፃናትን ስርአት ማስተማር እንደሚገባ በተለይ በሰውዬው ሀላፊነት ስር ያለን ልጅ ስርአት ማስተማር እንደሚገባ እንረዳለን።
- ህፃናትን በማስተማርና ስርአት በማስያዙ ረገድ የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እዝነትና ልበ ሰፊነትን እንረዳለን።
- ከፊቱ ካለው መመገብ ከአመጋገብ ስርአቶች መካከል አንዱ ነው። የምግብ አይነቶቹ ብዙ የሆኑ ጊዜ ግን ከፊቱ ውጪ ካለ መውሰድም ይችላል።
- ሶሐቦች ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያስተማሯቸውን ስርአት አጥብቀው መያዛቸውን እንረዳለን። ይህንንም ነጥብ "ከዛን ጊዜ በኋላ ከዚህ የአበላል ስርአት አልተወገድኩም።" ከሚለው የዑመር ንግግር እንረዳለን።