- አንድ ሙስሊም ለነፍሱ የሚወደውን ነገር ለወንድሙ የመውደድ ግዴታ እንዳለበት እንረዳለን። ለነፍሱ የሚወደውን ነገር ለወንድሙ የማይወድ ሰው ላይ ኢማን ውድቅ መደረጉ ይህን መተግበር ግዴታ መሆኑን ይጠቁማልና።
- ለአላህ ብሎ ወንድማማች መሆን ከዘር ወንድማማችነትም በላይ ነው። የኢስላማዊ ወንድማማችነት ግዴታውም የበለጠ ነው።
- ይህንን ውዴታ የሚቃረን ሁሉ ማጭበርበር፣ ሀሜት፣ ምቀኝነት፣ በሙስሊም ነፍስ ላይ ወይም ገንዘቡ ላይ ወይም ክብሩ ላይ ጠላት መሆንን የመሳሰሉ ንግግርም ሆነ ተግባርም ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
- "ለወንድሙ" ከሚለው ቃል ለአንድ ተግባር የሚያነሳሳ የሆነን ቃል መጠቀም እንደሚገባ እንረዳለን።
- ኪርማኒ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል: «ከዚህም በተጨማሪ ለነፍሱ የሚጠላውን መጥፎ ነገር ለወንድሙ መጥላቱም የኢማን ክፍል ነው። ሐዲሡ ላይ ያልጠቀሱት አንድን ነገር መውደድ ተቃራኒውን መጥላት የሚያስፈርድ ስለሆነ በዚህ በመብቃቃት መጥቀሱን ተዉት።