- የአንድ አማኝ ግዴታ ሰዎች አላህን እንዲወዱ ማድረግና በመልካም ነገሮች ላይ ማነሳሳት ነው።
- ወደ አላህ የሚጣራ ሰው የኢስላምን ጥሪ ወደ ሰዎች በጥበብ እንዴት እንደሚያደርስ ማስተዋል ይገባዋል።
- ማበሰር ለዳዒውም ለሚያስተላልፈው ነገርም ደስታን ተሰሚነትንና መረጋጋትን ያስተርፋል።
- ማካበድ በዳዒው ንግግር ውስጥ ማሸሽን ፣ ተቀባይነት ማጣትና ጥርጣሬን ይፈጥራል።
- ለነርሱ የወደደላቸው ገር እምነትና ቀላል ድንጋጌ በመሆኑ አላህ በባሮቹ ላይ ያለው እዝነት ሰፊ መሆኑን እንረዳለን።
- እንድናግራራ የታዘዝንባቸውን ነገሮች ማግራራት ሸሪዓ ይዞት የመጣው አንዱ ድንጋጌ ነው።