ከዑቅበህ ቢን ዓሚር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ሴቶች ጋር ከመግባት ተጠንቀ...
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከእንግዳ ሴቶች ጋር ከመቀላቀል እንዲህ በማለት አስጠነቀቁ "በሴቶች ላይ ከመግባትና ሴቶችም እናንተ ዘንድ እንዳይገቡ ነፍሳችሁን ጠብቁ!" አንድ የአንሷር...

ከዑቅበህ ቢን ዓሚር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ሴቶች ጋር ከመግባት ተጠንቀቁ!" አንድ ከአንሷር የሆነ ሰውዬም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ስለባል ቅርብ ዘመዶች ንገሩኝ እስኪ?" አለ። እርሳቸውም "የባል ቅርብ ዘመድማ ሞት ነው።" አሉ።

ከአቡ ሙሳ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ፦ "ያለ ወሊይ ፈቃድ ጋብቻ የለም።"

የአማኞች እናት ከሆነችው ከዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ከወሊዩዋ (አሳዳጊዋ) ፈቃድ ውጪ ያገባች ማንኛዋም ሴት ጋባቻዋ ውድቅ ነው። (ንግግራቸውን ሶስት ጊዜ ደጋግሙት) እርሷን ከተገናኘም በመንካቱ ምክንያት መህሯ የራሷ ነው። ወሊዮች ከተጨቃጨቁም ወሊይ ለሌለው ሰው የሙስሊሞች መሪ ወሊዩ ነው።"»

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ሚስቱን በመቀመጫዋ የተገናኛት ሰው የተረገመ ነው።"»

ከዑቅበህ ቢን ዓሚር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: 'ልታሟሉት ከሚገቡ መስፈርቶች ሁሉ ልታሟሉት እጅግ የተገባው ብልትን ሐላል ያደረጋቹበትን መስፈርት ነው።'"

ከዐብደላህ ቢን ዐምር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "ዱንያ መጣቀሚያ ናት። ከዱንያ መጣቀሚያዎች ምርጡ መልካም ሚስት ናት።"

ከጀሪር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ «የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለድንገተኛ እይታ ጠየቅኳቸው። እርሳቸውም አይኔን እንዳዞር አዘዙኝ።»

ከአነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለኡዱሒያ ሁለት ቡራቡሬና ቀንዳም የሆኑ ሙክቶችን በእጃቸው አረዱ። "ቢስሚላህ አላሁ አክበር" አሉና እግራቸውን አንገቱ ላይ አድርገው አረዱት።»

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦ "የሙስሊም ሽርጥ እስከ ባቱ ግማሽ ድረስ ነው። ከባቱ ግማሽና በቁርጭምጭሚቱ መሃል ቢሆንም ግን ችግር የለውም። ከቁርጭምጭሚት ዝቅ ያለ ከሆነ እርሱ እሳት ውስጥ ነው። ሽርጡን በኩራት የጎተተን ሰው አላህ ወደርሱ አይመለከትም።"

ከዐብዱረሕማን ቢን አቢ ለይላ እንደተላለፈው እነርሱ ሑዘይፋ ዘንድ ነበሩ። የሚጠጣ እንዲሰጡት ሲጠይቅ አንድ እሳት አምላኪ የሚጠጣ (በብር እቃ) ሰጠው። እቃውን (በሑዘይፋ) እጁ ላይ ሲያኖረውም በርሱ ወረወረበትና እንዲህ አለ: "ከአንድና ሁለት ጊዜ በላይ ባልከለክለው ኖር ‐ ይህን አላደርግም ነበር ‐ ነበር። ነገር ግን ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "የቀጭን ሐርንና የወፍራም ሐርን ልብስ አትልበሱ! በወርቅና ብር እቃ አትጠጡ! በ(ወርቅና ብር) ትሪም አትብሉ! እርሷ በዚህ ዓለም ለነርሱ ናት፤ በመጪው ዓለም ደግሞ ለኛ ናት።"

ከዐሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ከሶስት ዓይነት አካላት ላይ ብእር ተነስቷል። የተኛ ሰው እስኪነቃ ድረስ፤ ህፃን ልጅ አቅመ አዳም እስኪደርስ ድረስ እና እብድ ጤነኛ እስኪሆን ድረስ ነው።"

ከኢብኑ ዑመር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፀጉርን አንዱን ተላጭቶ አንዱን ትቶ ከመቆረጥ ከልክለዋል።"