ከዐብደላህ ቢን ዑመር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ተልቢያቸው "ለበይከ አልላሁምመ ለበይክ፣ ለበይከ ላ ሸሪከ ለከ ለበይክ፣ ኢነል...
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ወደ ሐጅ ወይም ዑምራ ተግባር መግባት ሲፈልጉ ይሉት የነበረው ተልቢያ እንዲህ ብለው ነበር: (ለበይከ አልላሁመ ለበይክ) አላህ ሆይ! ወደ ጠራኸን ተውሒድ፣ ስራን ለአላህ ማጥራት፣ ለሐ...
ከኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: 'ከነዚህ ቀናቶች የበለጠ መልካም ስራዎች ወደ አላህ ተወዳጅ የሚሆኑበት ምንም ቀን የለም።' ማለት...
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በዙልሒጃ ወር የመጀመሪያ አስር ቀናቶች ውስጥ መልካም ስራዎችን መስራት በአመቱ ውስጥ ከሚገኙ ቀናቶች ሁሉ የበለጠ መሆኑን ገለፁ። ሰሐቦችም አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና ነቢዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወ...
ከአነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "አጋርያንን በገንዘባችሁ፣ በነፍሳችሁና በምላሳችሁ ታ...
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የአላህ ንግግር የበላይ እንድትሆን በተቻለ መጠን በሁሉም መንገድ ከሃዲያንን ለመታገልና እነርሱን ለመጋፈጥ በአቅም ልክ መታገልን አዘዙ። ከነዚህም መታገያዎች...
ከአቡል ሐውራእ አስሰዕዲይ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: ለሐሰን ቢን ዐሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - «ከአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ምን...
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ክልክል ነው ወይስ አይደለም፣ ሐላል ነው ወይስ ሐራም ነው እያልክ የምትጠራጠርበት ንግግርና ተግባር በመተው መልካምነቱንና ፍቁድነቱን እርግጠኛ ወደሆንክበትና...
ከአቡ ሁረይራ (ዲዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "አላህ ከኡመቴ በውስጣቸው የሚናገሩትን ነገር...
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ ወንጀልነቱን ስላነሳና ይቅር ስላለ አንድ ሙስሊም በውስጡ አስቦ ለተወው መጥፎ ነገር እስካልሰራበት ወይም እስካልተናገረው ድረስ እንደማይያዝበት ተናገሩ።...

ከዐብደላህ ቢን ዑመር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ተልቢያቸው "ለበይከ አልላሁምመ ለበይክ፣ ለበይከ ላ ሸሪከ ለከ ለበይክ፣ ኢነልሐምደ ወንኒዕመተ ለከ ወልሙልክ ላ ሸሪከ ለክ" (አላህ ሆይ! ደግሜ ደጋግሜ ለጥሪህ አቤት እላለሁ፤ ምንም ተጋሪ የለህም። ምስጋና ፀጋና ንግስና ለአንተ ብቻ ነው፤ ምንም ተጋሪ የለህም።) የሚል ነበር። ዐብደላህ ቢን ዑመር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እዚህ ላይ "ለበይከ ለበይከ ወሰዕደይክ፣ ወልኸይሩ ቢየደይክ፣ ለበይከ ወርረግባኡ ኢለይከ ወልዐመል" (ጥሪህን ተቀብያለሁ፣ ለጥሪህ ምላሽ እሰጣለሁ፣ መልካም ነገር ሁሉ በእጅህ ነው፤ ምኞትና ተግባር ወደ አንተ ይመራል።) የሚለውን ይጨምሩ ነበር።»

ከኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: 'ከነዚህ ቀናቶች የበለጠ መልካም ስራዎች ወደ አላህ ተወዳጅ የሚሆኑበት ምንም ቀን የለም።' ማለትም አስሩ የዙልሂጃ ቀናቶች ናቸው። ሰሐቦችም 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! በአላህ መንገድ ጂሃድ ማድረግም ቢሆን?' በማለት ጠየቁ። እሳቸውም 'በአላህ መንገድ ጂሃድም ቢሆን እንኳ (አይበልጥም) ነፍሱና ገንዘቡን ይዞ የወጣና ከነዚህ መካከል አንዱም ያልተመለሰለት ሙጃሂድ ሲቀር' አሉ።"

ከአነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "አጋርያንን በገንዘባችሁ፣ በነፍሳችሁና በምላሳችሁ ታገሉ።"

ከአቡል ሐውራእ አስሰዕዲይ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: ለሐሰን ቢን ዐሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - «ከአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ምን ሸምድደሃል? አልኩት። እርሱም: "ከአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ይህን ሸምድጃለሁ አለኝ። ‹የሚያጠራጥርህን ነገር ተውና ወደ ማያጠራጥርህ ሂድ! እውነት እርጋታን የተላበሰ ነው። ውሸት ደሞ ጥርጣሬን የተላበሰ ነው።›"»

ከአቡ ሁረይራ (ዲዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "አላህ ከኡመቴ በውስጣቸው የሚናገሩትን ነገር እስካልሰሩት ወይም እስካልተናገሩት ድረስ ይቅር ብሏቸዋል።"

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወስለም እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ ወደ ቅርፃችሁና ገንዘቦቻችሁ አይመለከትም ነገር ግን ወደ ልቦቻችሁና ስራዎቻችሁ ይመለከታል።"

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: ‹አላህ ይቀናል። የአላህ መቅናት ሰውዬው አላህ በሱ ላይ ክልክል ያደረገበትን ሲዳፈር ነው።›"

አቢ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ማለታቸውን አስተላልፈዋል፡ "ሰባት አጥፊዎችን ተጠንቀቁ!" ሶሓቦችም: "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ምን ምን ናቸው?" ብለው ጠየቁ፥ ነቢዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "በአላህ ማጋራት፣ ድግምት፣ አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ በአግባቡ ካልሆነ በስተቀር መግደል፣ አራጣ መብላት፣ የየቲምን ገንዘብ መብላት፣ ጦርነት በተፋፋመ እለት ማፈግፈግ፣ ከዝሙት ዝንጉ የሆኑ ጥብቅ ምእመናትን በዝሙት መዝለፍ ናቸው።" አሉ።

ከአቢ በክረህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሶስት ጊዜ እንዲህ አሉ፦ "'ከትልልቅ ወንጀሎች ትልቁን አልነግራችሁምን?' እኛም 'እንዴታ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ!' አልናቸው። እሳቸውም፦ 'በአላህ ማጋራት ፣ የወላጆችን ሐቅ ማጓደል' አሉ። ደገፍ ብለው ከነበረበትም ተስተካክለው ተቀመጡና 'ንቁ! የውሸት ንግግርን (ተጠንቀቁ)።' አሉ። ምነው ዝም ባሉ እስክንል ድረስም ይህንን ከመደጋገም አልተወገዱም።"

ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን አልዐስ (ረዲየሏሁ ዓንሁማ) አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "ትላልቅ ወንጀሎች፦ በአላህ ማጋራት፣ የወላጆችን ሐቅ ማጓደል፣ ነፍስ ማጥፋትና የውሸት መሀላ ናቸው።"

ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: «የትንሳኤ ቀን በሰዎች መካከል መጀመሪያ የሚፈረደው ጉዳይ የደም ጉዳይ ነው።»

ከዐብደሏህ ቢን ዓምር (ረዲየሏሁ ዓንሁማ) አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ማለታቸው ተላልፏል፡ "በቃል ኪዳን ስር ያለን (ሙዓሀድን) የገደለ ሰው የጀነትን ሽታ አያሸትም። የጀነት ሽታዋ የሚገኘው አርባ አመት ከሚያስኬድ ርቀት በኃላ ነው።"