/ የትንሳኤ ቀን በሰዎች መካከል መጀመሪያ የሚፈረደው ጉዳይ የደም ጉዳይ ነው።

የትንሳኤ ቀን በሰዎች መካከል መጀመሪያ የሚፈረደው ጉዳይ የደም ጉዳይ ነው።

ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: «የትንሳኤ ቀን በሰዎች መካከል መጀመሪያ የሚፈረደው ጉዳይ የደም ጉዳይ ነው።»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የትንሳኤ ቀን በሰዎች መካከል መጀመሪያ የሚፈረደው ጉዳይ ከፊሉ ከፊሉን የሚበድልበት በሆነው እንደመግደልና ማቁሰል ያሉ የደም ጉዳዮች መሆኑን አወሱ።

Hadeeth benefits

  1. የደም ጉዳይ ከባድ መሆኑን እንረዳለን። ፍርድ የሚጀመረው በአንገብጋቢው ጉዳይ ነውና።
  2. ወንጀሎች የሚተልቁት በርሱ ምክንያት የሚከሰቱ ብክለቶች እንደመተለቃቸው መጠን ነው። ንፁህ ነፍስን ማጥፋት ደሞ ከትላልቅ ብክለቶች መካከል አንዱ ነው። በአላህ ማጋራትና ኩፍር (ክህደት) እንጂ ምንም ከርሱ የሚከፋ ወንጀልም የለም።