- ሐጅና ዑምራ ላይ ተልቢያ የተደነገገ መሆኑንና አፅንዖት የተሰጠው መሆኑን እንረዳለን። ተክቢራ የሶላት መገለጫ እንደሆነው ሁሉ ተልቢያም በሐጅና ዑምራ ወቅት ልዩ መገለጫው ነው።
- ኢብኑል ሙኒር እንዲህ ብለዋል: "ተልቢያ መደንገጉ አላህ ባሮቹን ምን ያህል እንዳከበረ ያስገነዝበናል። ይህም ወደ ቤቱ ጉብኝት ማድረጋቸው በአላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ጥሪ እንደሆነ ስለሚጠቁም ነው።"
- በላጩ ተልቢያ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ያደረጉትን ተልቢያ ማለት ነው። ቢጨምርም ግን ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ያፀደቁት ስለሆነ ችግር የለውም። ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሚዛናዊው መንገድ ነው። ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የመጣውን ለብቻው ይልና ከሶሐባ የመጣን ወይም ቦታው ላይ የሚመጥን በራሱ ማለት የሚፈልገውን ለማለት የፈለገ ጊዜ ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከመጣው ጋር በማይቀላቀል መልኩ ለብቻው ይለዋል። ይህ ተልቢያ ተሸሁድ ላይ ከመጣው ዱዓ ጋር ይመሳሰላል። ነቢዩ በተሸሁድ ዱዓ ዙሪያ እንዲህ ብለዋል፡ "ከዚያም የሻውን ዱዓና ውዳሴ ይምረጥ።" ማለትም ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የመጣውን ከጨረሰ በኋላ ነው።"
- በተልቢያ ድምፅን ከፍ ማድረግ እንደሚወደድ እንረዳለን። ይህም ለወንድ ነው። ሴት ከሆነች ግን ፈተናን ስለሚያሰጋ ድምጿን ዝግ ታደርጋለች።