- ቀልብን ከሁሉም ውግዝ ባህሪያት ማስተካከልና ማፅዳት ላይ ትኩረት መስጠት እንዳለብን፤
- ቀልብ የሚስተካከለው በኢኽላስ ሲሆን ስራ የሚስተካከለው ደግሞ ነቢዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በመከተል ነው። አላህ ዘንድ ትኩረት የሚቸራቸውና ግምት ውስጥ የሚገቡት እነዚህ ሁለቱ ናቸው።
- የሰው ልጅ በገንዘቡም፣ በውበቱም፣ በሰውነቱም ሆነ በዚህች ዓለማዊ መገለጫዎች በአንዳችም ነገር መሸወድ እንደሌለበት ፤
- ውስጣዊ ማንነትን ሳያስተካክሉ ውጫዊ የሆኑ መገለጫዎችን ከመደገፍ መጠንቀቅ እንዳለብን ተረድተናል።