- አላህ ተባረከ ወተዓላ በነፍስ ላይ የምትመጣንና ሰውዬው በውስጡ የሚናገራትንና ውል የምትልበትን አስተሳሰብና ሹክሹክታ ይቅር ብሏልም አልፏልም።
- አንድ ሰው ሚስቱን መፍታት ቢያስብና በውስጡ ውል ቢልበትም ነገር ግን ካልተናገረና ካልፃፈው ፍቺ ተደርጎ አይቆጠርበትም።
- በውስጥ የሚወራ ወሬ ምንም ያህል ቢገዝፍ በውስጡ እስካልፀና፣ በርሱ እስካልሰራ ወይም እስካልተናገረ ድረስ አይያዝበትም።
- የሙሐመድ ኡመት (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከኛ በፊት ከነበሩት ህዝቦች በተቃራኒ ከራሳቸው ጋር በውስጥ በማውራታቸው ባለመያዝ የተለዩ መሆናቸው ደረጃቸው የላቀ መሆኑን ያስረዳናል።