- የውሸት መሀላ አደገኝነቱና ወንጀልነቱ ከባድ ከመሆኑ አንፃር ተውበት እንጂ ምንም ማካካሻ የለውም።
- ሐዲሡ ውስጥ እነዚህ አራት ወንጀሎች ብቻ መጠቀሳቸው ወንጀልነታቸው ከባድ ስለሆነ እንጂ የቁጥር ገደብ አይደለም።
- ወንጀሎች ወደ ትላልቅና ትናንሽ ይከፈላሉ። ትላልቅ የሚባሉት: ማንኛውም አለማዊ ቅጣት የተቀመጠለት ወንጀል ለምሳሌ :- ቅጣቱ በሸሪዓዊ መቅጫ ህግ ውስጥ ያለ (ሑዱድ)፣ መረጋገም ያለበት፤ ወይም እሳት መግባትን የመሰለ አኺራዊ ዛቻ የመጣበት ናቸው። ትላልቅ ወንጀሎች የተለያዩ ደረጃዎች አላቸው። የክልከላ ደረጃውም ከፊሉ ከከፊሉ ይከብዳል። ትናንሽ ወንጀሎች የሚባሉት ደግሞ ከትላልቅ ወንጀሎች ውጪ ያሉት ናቸው።