- ሙስሊም የሆነ ሰው ጉዳዮቹን በርግጠኝነት ላይ መመስረት አለበት። የሚጠራጠርበትን ነገር ትቶ በሃይማኖቱም እውቀት ላይ መሆን አለበት።
- አጠራጣሪ ነገር ላይ ከመውደቅ መከልከሉን እንረዳለን።
- እርጋታና እረፍትን ከፈለግክ አጠራጣሪ ነገርን ትተህ ወደ ጎን መጣል አለብህ።
- አላህ ለባሮቹ ነፍሳቸውና ሀሳባቸው እረፍት የሚያገኝበትን ማዘዙና ጭንቀትና መዋለል ውስጥ ከሚከታቸው ነገርም መከልከሉ ለነርሱ ያለውን እዝነት ያስረዳናል።