- ከከሀዲያን መካከል "ሙዓሀድን" ፣ "ዚሚይን" እና "ሙስተእመንን" መግደል ክልክልና ከትላልቅ ወንጀል የሚመደብም ነው።
- "ሙዓሀድ" ማለት: ከከሀዲያን መካከል በሀገሩ እየኖረ ሙስሊሞችን ላይዋጋ እነሱም ላይዋጉት ከሙስሊሞች ጋር ቃል ኪዳን የተጋባ ነው።
- "ዚሚይ" ማለት: በሙስሊሞች ሀገር እንደሀገሩ እየኖረ ግብር የሚከፍል ነው።
- "ሙስተእመን" ማለት ደግሞ ለተወሰነ ወቅት በቃል ኪዳንና ደህንነት ከለላ ወደ ሙስሊሞች ሀገር የገባ ሰው ነው።
- ከሙስሊሞች ውጪ ካሉ ጋር ቃል ኪዳንን ማፍረስ መከልከሉን እንረዳለን።