- እጅግ ትልቁ ወንጀል በአላህ ላይ ማጋራት ነው። ምክንያቱም ሐዲሡ ላይ ከትላልቅ ወንጀሎች ሁሉ ግንባር ቀደምና ትልቁ አድርገው ጠቀሰውታልና። ይህንንም {አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍፁም አይምርም። ከዚህ ሌላ ያለውንም (ሀጢዐት) ለሚሻው ሰው ይምራል።} የሚለው የአላህ ንግግር ያጠናክረዋል።
- ሐዲሡ ላይ የወላጆች ሐቅ ከአላህ ሐቅ ጋር በመቆራኘቱ የወላጆችን ሐቅ ታላቅነት እንረዳለን።
- ወንጀሎች ወደ ትላልቅና ትናንሽ ይከፈላሉ። ትላልቅ የሚባሉት: ማንኛውም አለማዊ ቅጣት የተቀመጠለት ወንጀል ለምሳሌ :- ቅጣቱ በሸሪዓዊ መቅጫ ህግ ውስጥ ያለ (ሑዱድ)፣ መረጋገም ያለበት፤ ወይም እሳት መግባትን የመሰለ አኺራዊ ዛቻ የመጣበት ናቸው። ትላልቅ ወንጀሎች የተለያዩ ደረጃዎች አላቸው። የክልከላ ደረጃውም ከፊሉ ከከፊሉ ይከብዳል። ትናንሽ ወንጀሎች የሚባሉት ደግሞ ከትላልቅ ወንጀሎች ውጪ ያሉት ናቸው።