- አጋርያንን በነፍስ፣ በገንዘብና በምላስ መታገል ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። ሁሉም በአቅሙ ልክ ነው። ጂሃድ በአካል በመዋጋት ላይ ብቻ የተገደበ አይደለምና።
- በጂሃድ የመጣው ትእዛዝ ግዴታን ነው የሚጠቁመው። አንዳንዴ በነፍስ ወከፍ ደረጃ ግዴታ ሲሆን አንዳንዴ ደግሞ በተወሰነ አካል ላይ ብቻ ግዴታ ይሆናል።
- አላህ ጂሃድን ለብዙ ጉዳዮች ደንግጓል: ከነርሱም መካከል: የመጀመሪያ: ሺርክንና አጋርያንን መቃወም። አላህ መቼም ሺርክን አይቀበልምና። ሁለተኛ: ወደ አላህ በሚደረግ ደዕዋ መንገድ የሚጋረጡ ሳንካዎችን ማስወገጃ ነው። ሶስተኛ: የእስልምናን እምነት ከሚፃረሩት ሁሉ ነገሮች መጠበቂያ ነው። አራተኛ: ከሙስሊሞች፣ ከሀገራቸው፣ ከክብራቸውና ከገንዘባቸው መከላከያ ነው።