ዋና ገፅ
እኛ ማን ነን
am
English
العربية
español
português
Français
Русский
اردو
azərbaycanca
Ўзбек
Deutsch
Shqip
فلبيني مرناو
براهوئي
български
বাংলা
ဗမာ
bosanski
polski
தமிழ்
ไทย
татар теле
română
isiZulu
سنڌي
සිංහල
Kiswahili
svenska
нохчийн мотт
Soomaali
тоҷикӣ
غجري
Pulaar
Pulaar
Tiếng Việt
قمري
कश्मीरी
한국어
македонски
bahasa Melayu
മലയാളം
magyar
हिन्दी
Hausa
Èdè Yorùbá
ελληνικά
қазақ тілі
فارسی
Türkçe
עברית
中文
Bahasa Indonesia
Wikang Tagalog
dansk
پښتو
Tamazight
አማርኛ
أنكو
ئۇيغۇرچە
Luganda
తెలుగు
日本語
ትግርኛ
غموقي
Кыргызча
नेपाली
Kurdî
italiano
Nederlands
čeština
українська
eesti
suomi
Адыгэбзэ
Norwegian
latviešu
slovenščina
монгол
íslenska
ქართული
tamashaq
ދިވެހި
Հայերէն
slovenčina
Afrikaans
Türkmençe
башҡорт теле
afaan oromoo
ភាសាខ្មែរ
ಕನ್ನಡ
Bassa
Lingala
lietuvių
bamanankan
Soninke
Malagasy
Mandinka
Sängö
Wollof
Cham
Qhichwa simi
Српски
Afaraf
hrvatski
Kinyarwanda
aymar aru
Jóola
Bi zimanê Kurdî
Akan
ଓଡ଼ିଆ
Chichewa
авар мацӀ
Igbo
isiXhosa
मराठी
Fɔ̀ngbè
ગુજરાતી
Mɛnde
ГӀалгӀай
Mõõré
অসমীয়া
Maguindanao
Dagbani
Yao
Ikirundi
Bisaya
Ruáingga
فارسی دری
Sesotho
ਪੰਜਾਬੀ
créole
ພາສາລາວ
ዋና ገፅ
እኛ ማን ነን
Contact Us
ከጁበይር ቢን ሙጥዒም -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እሱ ነቢዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰማቸው: "ዝምድናን ቆራጭ ጀነት አይገባም።"
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለቅርብ ዘመዶቹ ያለበትን ግዴታ ከመወጣት ይልቅ ዝምድናውን የቆረጠ ሰው ወይም ያወካቸውና ያስከፋቸው ጀነት ላለመግባት የተገባ ነው ብለው ተናገሩ።
ከአነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "ሲሳዩ እንዲሰፋለትና እድሜው እንዲረዝምለት የወደደ ሰው ዝምድናውን ይቀጥል።"
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቅርብ ዘመዶችን በመዘየር ፣ በአካላዊና ገንዘባዊ ጉዳይ በማገዝና በሌሎችም መልኩ ዝምድናን በመቀጠል ላይ አነሳሱ። በተጨማሪም ዝምድናን መቀጠል ለሲሳይ መስፋትና ለእድሜ መርዘም ምክንያት መሆኑንም ተናገሩ።
ከዐብደሏህ ቢን ዐምር ረዲየሏሁ ዐንሁማ እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፡ "ዝምድና ቀጣይ የሚባለው ላደረጉለት መልካም ነገር ምላሹን የሚሰጥ የሆነው አይደለም፤ ይልቁንም ዝምድና ቀጣይ የሚባ...
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እየነገሩን ያሉት ዝምድናን በመቀጠል የተሟላና ለዘመዶቹም በጎ ሰሪ የሚባለው ላደረጉለት መልካም ነገር መልካሙን በመመለስ የተብቃቃው አይደለም፤ ይልቁንም ዝምድናውን በመቀጠል በኩል የተሟላ...
ከበህዝ ቢን ሐኪም ከአባቱ እንደተላለፈው: አባቱም ከአያቱ እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ: «"የአላህ መልክተኛ ሆይ! በጎ ላደርግለት እጅግ የተገባው ማን ነው?" አልኳቸው። እርሳቸውም "እናትህ ከዚያም እናትህ ከዚያም እናትህ ከዚያም አባትህ...
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከሰዎች ሁሉ አስበልጠን በጎ ሊዋልለት፣ መልካም ሊሰራለት የሚገባው፣ ባማረ መልኩ ልንኗኗረው፣ ልንወዳጀውና ትስስራችንን ልናጠናክርለት የሚገባው በላጩ ሰው ማን እንደሆነ ገለፁ። እርሷ...
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ፡ "ሀሜት ምን እንደሆነ ታውቃላችሁን?" ሶሐቦችም "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ።" አሉ። እሳቸውም "ወንድምህን በሚጠ...
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የተከለከለውን ሀሜት እውነታ : ሙስሊምን በሌለበት በሚጠላው ነገር ማውሳት መሆኑን አብራሩ። ይህም ተፈጥሯዊውም ሆነ ስነ ምግባሪያዊ ባህሪውን ቢያወሳ ተመሳሳይ ነው። እውሩ ፣ አጭበርባሪ ፣ ውሸታምና የመሳሰሉት...
ዝምድናን ቆራጭ ጀነት አይገባም።
ከጁበይር ቢን ሙጥዒም -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እሱ ነቢዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰማቸው: "ዝምድናን ቆራጭ ጀነት አይገባም።"
Hadeeth details
ሲሳዩ እንዲሰፋለትና እድሜው እንዲረዝምለት የወደደ ሰው ዝምድናውን ይቀጥል።
ከአነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "ሲሳዩ እንዲሰፋለትና እድሜው እንዲረዝምለት የወደደ ሰው ዝምድናውን ይቀጥል።"
Hadeeth details
ዝምድና ቀጣይ የሚባለው ላደረጉለት መልካም ነገር ምላሹን የሚሰጥ የሆነው አይደለም፤ ይልቁንም ዝምድና ቀጣይ የሚባለው ዝምድናው በተቆረጠ ጊዜ የሚቀጥል የሆነው ነው።...
ከዐብደሏህ ቢን ዐምር ረዲየሏሁ ዐንሁማ እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፡ "ዝምድና ቀጣይ የሚባለው ላደረጉለት መልካም ነገር ምላሹን የሚሰጥ የሆነው አይደለም፤ ይልቁንም ዝምድና ቀጣይ የሚባለው ዝምድናው በተቆረጠ ጊዜ የሚቀጥል የሆነው ነው።"
Hadeeth details
የአላህ መልክተኛ ሆይ! በጎ ላደርግለት እጅግ የተገባው ማን ነው?" አልኳቸው። እርሳቸውም "እናትህ ከዚያም እናትህ ከዚያም እናትህ ከዚያም አባትህ ከዚያም ቅርብ የሆኑ ዘመዶችህ" አሉ።...
ከበህዝ ቢን ሐኪም ከአባቱ እንደተላለፈው: አባቱም ከአያቱ እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ: «"የአላህ መልክተኛ ሆይ! በጎ ላደርግለት እጅግ የተገባው ማን ነው?" አልኳቸው። እርሳቸውም "እናትህ ከዚያም እናትህ ከዚያም እናትህ ከዚያም አባትህ ከዚያም ቅርብ የሆኑ ዘመዶችህ" አሉ።»
Hadeeth details
ሀሜት ምን እንደሆነ ታውቃላችሁን?" ሶሐቦችም "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ።" አሉ። እሳቸውም "ወንድምህን በሚጠላው ነገር ማውሳትህ ነው።
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ፡ "ሀሜት ምን እንደሆነ ታውቃላችሁን?" ሶሐቦችም "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ።" አሉ። እሳቸውም "ወንድምህን በሚጠላው ነገር ማውሳትህ ነው።" አሉ። "የምናገረው ነገር ወንድሜ ላይ ካለስ (ሀሜት ይባላልን?)" ተብለው ተጠየቁ። እሳቸውም "የምትናገረው ነገር እሱ ላይ ካለ በርግጥ አምተሀዋል። እሱ ላይ ከሌለ ደግሞ በርግጥም ቀጥፈህበታል።"
Hadeeth details
አስካሪ ሁሉ ኸምር ነው። አስካሪ ሁሉ ክልክል ነው። በዚህ ዓለም አስካሪ መጠጥ አዘውትሮ ጠጥቶ ንስሀ ሳይገባ የሞተ ሰው በመጪው ዓለም አይጠጣም።
ከኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አስካሪ ሁሉ ኸምር ነው። አስካሪ ሁሉ ክልክል ነው። በዚህ ዓለም አስካሪ መጠጥ አዘውትሮ ጠጥቶ ንስሀ ሳይገባ የሞተ ሰው በመጪው ዓለም አይጠጣም።"»
Hadeeth details
የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በፍርድ አሰጣጥ ዙሪያ ጉቦ ሰጪንም ተቀባይንም ረገሙ።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በፍርድ አሰጣጥ ዙሪያ ጉቦ ሰጪንም ተቀባይንም ረገሙ።"
Hadeeth details
አትመቀኛኙ፤ (ገዢን ለመጉዳት) አትጫረቱ፤ አትጠላሉ፤ ጀርባ አትሰጣጡ፤ አንዳችሁ በአንዱ ገበያ ላይ አይሽጥ! የአላህ ባሮች ወንድማማቾች ሁኑ።
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦ "አትመቀኛኙ፤ (ገዢን ለመጉዳት) አትጫረቱ፤ አትጠላሉ፤ ጀርባ አትሰጣጡ፤ አንዳችሁ በአንዱ ገበያ ላይ አይሽጥ! የአላህ ባሮች ወንድማማቾች ሁኑ። ሙስሊም የሙስሊም ወንድም ነው። አይበድለው፤ እርዳታ አይንፈገው፤ አያሳንሰው።" ወደ ደረታቸው እየጠቆሙም ሶስት ጊዜ "አላህን መፍራት እዚህ ጋር ነው።" አሉ። "ሰውዬው ሙስሊም ወንድሙን አሳንሶ መመልከቱ መጥፎ ሠራ ለመባል ይበቃዋል። ሁሉም ሙስሊም በሌላ ሙስሊም ላይ ደሙ፣ ገንዘቡና ክብሩ እርም ነው።"
Hadeeth details
አደራችሁን ጥርጣሬን ተጠንቀቁ! ጥርጣሬ እጅግ ውሸት የሆነ ወሬ ነውና።
አቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ማለታቸውን አስተላልፈዋል: "አደራችሁን ጥርጣሬን ተጠንቀቁ! ጥርጣሬ እጅግ ውሸት የሆነ ወሬ ነውና። አትፈላፈሉ፣ አትሰልሉ፣ አትመቀኛኙ፣ ጀርባም አትሰጣጡ፣ አትጠላሉ (ይልቁንም) ወንድማማች የአላህ ባሮች ሁኑ።"
Hadeeth details
ነገር አዋሳጅ ጀነት አይገባም።
ከሑዘይፋ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: ነቢዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ: "ነገር አዋሳጅ ጀነት አይገባም።"
Hadeeth details
'ወንጀላቸውን ይፋ ከሚያደርጉ በስተቀር ሁሉም ህዝቦቼ ይማርላቸዋል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፦ 'ወንጀላቸውን ይፋ ከሚያደርጉ በስተቀር ሁሉም ህዝቦቼ ይማርላቸዋል። ይፋ ከማውጣትም መካከል ሰውዬው ምሽት ላይ አንድ ወንጀልን ይሰራል ከዚያም አላህ በርሱ ላይ (ወንጀሉን) ሸሽጎለት አንግቶ ሳለ ‹እከሌ ሆይ! ትናንት ምሽት እንዲህ እንዲህ ሰራሁ።› ይላል። ጌታው (ወንጀሉን) ሸሽጎለት አድሮ ሳለ የአላህን ግርዶሽ ከራሱ ላይ የሚገፍ ሆኖ ያነጋል።"
Hadeeth details
እናንተ ሰዎች ሆይ! አላህ ከናንተ ላይ የድንቁርና ዘመንን ኩራትና በአባቶች መኮፈስን አስወግዷል።
ከኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መካ የተከፈተ እለት ለሰዎች ኹጥባ አደረጉ። እንዲህም አሉ ' እናንተ ሰዎች ሆይ! አላህ ከናንተ ላይ የድንቁርና ዘመንን ኩራትና በአባቶች መኮፈስን አስወግዷል። ሰዎች ሁለት አይነት ናቸው። በጎ፣ አላህን ፈሪና አላህ ዘንድ የተከበረ፤ አመፀኛ፣ ጠማማና አላህ ዘንድ የወረደ ናቸው። ሰዎች የአደም ልጆች ናቸው። አላህም አደምን ከአፈር ነው የፈጠረው። አላህ እንዲህ ብሏል፦ {እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ። እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ። አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው። አላህ ግልፅን አዋቂ ውስጥንም አዋቂ ነው።} [ሑጁራት: 13]'"
Hadeeth details
‹
1
2
...
17
18
19
20
21
22
23
...
30
31
›
Share
Use the QR code to easily share the message of Islam with others
Copy Link
copied!
ተገናኘን
×
ስም
ኢሜይል
የጽሑፉ መልዕክት
ተገናኘን
×
መልክት በመላኪህ እናመሰግናለን ...አላህ ካለ እናየዋለን
Share