/ ዝምድናን ቆራጭ ጀነት አይገባም።

ዝምድናን ቆራጭ ጀነት አይገባም።

ከጁበይር ቢን ሙጥዒም -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እሱ ነቢዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰማቸው: "ዝምድናን ቆራጭ ጀነት አይገባም።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

ትንታኔ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለቅርብ ዘመዶቹ ያለበትን ግዴታ ከመወጣት ይልቅ ዝምድናውን የቆረጠ ሰው ወይም ያወካቸውና ያስከፋቸው ጀነት ላለመግባት የተገባ ነው ብለው ተናገሩ።

Hadeeth benefits

  1. ዝምድናን መቁረጥ ከትላልቅ ወንጀሎች መካከል አንዱ ነው።
  2. ዝምድናን መቀጠል በተለምዶ በሚታወቀው መልኩ ነው የሚሆነው። ቦታ፣ ዘመንና ሰዎቹ እንደመለያየታቸው ይለያያል።
  3. ዝምድናን መቀጠል በመዘየር፣ ሶደቃ በመስጠት፣ ለነርሱ በጎ በመዋል፣ ሲታመሙ በመጠየቅ፣ በመልካም በማዘዝ፣ ከመጥፎ በመከልከልና በሌሎችም መልኩ ይፈፀማል።
  4. ዝምድናው የሚቆረጠው ሰው እጅግ ቅርብ ዘመድ በሆነ ቁጥር ወንጀሉም እጅግ የከፋ ይሆናል።