- በመጥፎ የሚያስጠረጥር ምልክት ግልፅ የሆነበትን ሰው መጠራጠር ምንም አይጎዳም። አማኝ የሆነ ሰውም በመጥፎዎችና አመፀኞች እንዳይሸወድ ብልጥና ጮሌ መሆን ይገባዋል።
- በሐዲሱ የተፈለገው ነፍስ ውስጥ ፀንቶ በሚቆይ መልኩ (በጥርጣሬ) መወንጀል እና በጥርጣሬም ላይ ከመዘውተር ማስጠንቀቅ ነው። ነፍስ ላይ ባልፀና መልኩ መጠርጠር ከሆነ ግን ይህ ተጠያቂ አያደርግም።
- በሙስሊሙ ማህበረሰብ ውስጥ በሚገኙ ግለሰቦች መካከል ለመናቆርና ለመቆራረጥ ምክንያት የሚሆኑ እንደ መሰለል፣ መመቅኘትና የመሳሰሉት ነገሮች መከልከላቸውን እንረዳለን።
- በተቆርቋሪነትና በመዋደድ ረገድ ከሙስሊም ጋር ሊኖረን የሚገባው መስተጋብር ወንድማዊ መስተጋብር መሆን እንዳለበት መታዘዛችንን እንረዳለን።