- ሐዲሡ እናትን ማስቀደም እንደሚገባ ቀጥሎ አባትን ቀጥሎ ቅርብ ዘመዶችን እንደየቅርበታቸው ደረጃ ማስቀደም እንደሚገባ ያስረዳናል።
- የወላጆች ደረጃ በተለይ የእናት ደረጃ መገለፁን ተረድተናል።
- ሐዲሡ ውስጥ ለእናት በጎ መስራትን ሶስት ጊዜ ደጋገሙት። ይህም ለልጆቿ ያላት ችሮታ ከሌላው የሚበልጥ ስለሆነ፤ የእርግዝናን ቀጥሎ የመውለድን ቀጥሎ የማጥባትን ጭንቅ፣ ድካምና መከራ በማየት የምታሳልፍበት ጊዜ ስለሚበዛና በዚህም የምትሰቃየው ብቻዋን ስለሆነች ነው። ከዚያም ደግሞ የማነፁን ጉዳይ ከአባት ጋር ትጋራለች።