- ዝምድና በማለት የተፈለገው በአባትና በእናት በኩል ያሉ ቅርብ ሰዎች ናቸው። እጅግ ቅርብ ዘመድ በሆኑ ቁጥር በዛው ልክ መቀጠሉም የተገባ ይሆናል።
- ምንዳ በስራው አምሳያ ነው የሚሰጠው። ዝምድናውን በበጎና መልካምነት የቀጠለ ሰውን አላህም እድሜውና ሲሳዩን ይቀጥልለታል።
- ዝምድናን መቀጠል ለሲሳይ መስፋትና መዘርጋት እንዲሁም ለእድሜ መርዘም ምክንያት ነው። ምንም እንኳ የመሞቻ ቀኑና ሲሳዩ የተወሰነ ቢሆን ባለው ሲሳይና እድሜ በረከት ይሰፍንበታል። የተሰጠውን እድሜ ሌላው ከሚጠቀምበት በላይ ይጠቀምበታል። በርግጥ የሲሳይና እድሜ መጨመሩ እውነተኛ መጨመር ነውም ተብሏል። አላህ እጅግ አዋቂ ነው!