- ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እውቀትን ጥያቄያዊ በሆነ መንገድ ማስተላለፋቸውን ስናይ የሳቸው የማስተማር ስልት ውብ መሆኑን እንረዳለን ፤
- ሶሐቦች "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ።" ማለታቸውን ስናይ ከነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጋር ያላቸው አደብ ውብ መሆኑን እንረዳለን ፤
- ተጠያቂ ስለማያውቀው ነገር "አላህ ያውቃል።" ማለት እንዳለበት እንረዳለን ፤
- ሸሪዐ ሐቆችን በመጠበቅና በማህበረሰቡ መካከል ወንድማማችነትን በመፍጠር ማህበረሰቡን መጠበቁን እንረዳለን ፤
- ሀሜት እንደአስፈላጊነቱ በአንዳንድ ሁኔታዎች ላይ ካልሆነ በስተቀር ክልክል ነው። ከነዚህም ውስጥ: - በደልን ለመከላከል : ይህም "እከሌ በድሎኛል ወይም በኔ ላይ እንዲህ ፈፅሟል።" በማለት ተበዳይ ሀቁን ማስመለስ የሚችል ሰው ዘንድ የበደለውን በማውሳት ነው። በትዳር ጉዳይ ወይም በሽርክና ወይም በጉርብትናና በመሳሰሉት ጉዳይ ለማማከር ሰውዬውን ማማት ከሚፈቀዱት መካከል የሚመደብ ነው።