- የኸምር ክልክልነት ምክንያቱ ማስከሩ ነው። ስለዚህ ማንኛውም አይነት አስካሪ ክልክል ነው።
- አላህ አስካሪ መጠጥን የከለከለው ትላልቅ ጉዳትና ብልሽቶችን ስለያዘ ነው።
- ኸምርን ጀነት ውስጥ ሲሆን መጠጣቱ የድሎትና የእርካታ ማሟያ ነው።
- በዚህ አለም አስካሪ መጠጥ ከመጠጣት ነፍሱን ያላቀበ አላህ ጀነት ውስጥ ከመጠጣት ይከለክለዋል። ምንዳ የሚሆነው በሰራው ስራ አይነት ነውና።
- ከሞት በፊት ከወንጀሎች ንስሀ በማድረግ ላይ መቻኮል እንደሚገባ መነሳሳቱን እንረዳለን።