- አላህ በርሱ ላይ ከሸሸገለት በኋላ ወንጀልን ይፋ ማውጣት ፀያፍ መሆኑን እንረዳለን።
- ወንጀልን ይፋ ማድረግ በአማኞች መካከል ብክለት እንዲሰራጭ ያደርጋል።
- አላህ በዱንያ የሸሸገው ሰው በመጨረሻው አለምም ይሸሽገዋል። ይህም አላህ በባሮቹ ላይ ካለው እዝነት ስፋት ነው።
- በወንጀል የተፈተነ ሰው ወንጀሉን በራሱ ሸሽጎ ወደ አላህ መመለስ ይገባዋል።
- ወንጀላቸውን ይፋ የሚያደርጉ ሰዎች ወንጀል ትልቅ መሆኑን እንረዳለን። እነሱም ወንጀላቸውን ይፋ ማድረግን በማሰብ ለነፍሳቸው ይቅርታን ያስመለጡ ናቸው።