/ ዝምድና ቀጣይ የሚባለው ላደረጉለት መልካም ነገር ምላሹን የሚሰጥ የሆነው አይደለም፤ ይልቁንም ዝምድና ቀጣይ የሚባለው ዝምድናው በተቆረጠ ጊዜ የሚቀጥል የሆነው ነው።...

ዝምድና ቀጣይ የሚባለው ላደረጉለት መልካም ነገር ምላሹን የሚሰጥ የሆነው አይደለም፤ ይልቁንም ዝምድና ቀጣይ የሚባለው ዝምድናው በተቆረጠ ጊዜ የሚቀጥል የሆነው ነው።...

ከዐብደሏህ ቢን ዐምር ረዲየሏሁ ዐንሁማ እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፡ "ዝምድና ቀጣይ የሚባለው ላደረጉለት መልካም ነገር ምላሹን የሚሰጥ የሆነው አይደለም፤ ይልቁንም ዝምድና ቀጣይ የሚባለው ዝምድናው በተቆረጠ ጊዜ የሚቀጥል የሆነው ነው።"
ቡኻሪ ዘግበውታል።

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እየነገሩን ያሉት ዝምድናን በመቀጠል የተሟላና ለዘመዶቹም በጎ ሰሪ የሚባለው ላደረጉለት መልካም ነገር መልካሙን በመመለስ የተብቃቃው አይደለም፤ ይልቁንም ዝምድናውን በመቀጠል በኩል የተሟላ የሚባለው ዝምድናው በተቆረጠ ጊዜ የሚቀጥል፤ ሰዎቹ እየከፉበትም ለነርሱ መልካሙን በማድረግ ምላሽ የሚሰጣቸው የሆነ ነው።

Hadeeth benefits

  1. ዝምድናን መቀጠል ሲባል በሸሪዓ የሚፈለግበት ካንተጋ የተቆራረጡትን ስትቀጥል፤ የበደሉህን ይቅር ስትላቸው፤ የነፈጉህን ስትለግሳቸው እንጂ ብድር በመመለስ መልኩ ላደረጉልህ ነገር ተመሳሳዩን ምላሽ መስጠትህ አይደለም።
  2. ዝምድናን መቀጠል የሚፈፀመው በገንዘብ፣ በዱዓእ፣ መልካሙን በማዘዝና ከመጥፎ በመከልከል ረገድ እና መሰል በሆኑ ነገራቶች ለነርሱ በጎ በማድረግ እንዲሁም ክፋትን ከነርሱ በተቻለ መጠን በማስወገድ ነው።