- እምነታዊ ወንድማማችነትን የሚያጠናክሩ ነገሮች ሁሉ መታዘዛቸው፤ እምነታዊ ወንድማማችነትን የሚያፈርሱ ንግግሮችና ተግባሮችም መከልከላቸውን እንረዳለን።
- አላህን የመፍራት መሰረቱ ቀልብ ውስጥ ያለው አላህን ማወቅ፣ እርሱን መፍራትና እርሱን መጠባበቅ ነው። መልካም ስራዎች የሚመነጩትም በዚህ ሁኔታ አላህን ከመፍራት ነው።
- ግልፅ የሆነ ጥመት የቀልብ ፍራቻ መድከሙን ይጠቁማል።
- በማንኛውም መልኩ በንግግርም ሆነ በተግባር ሙስሊምን ከማወክ መከልከሉን እንረዳለን።
- አንድ ሙስሊም የሌላ ሰው ፀጋ መወገዱን ሳይመኝ እንደሌላ ሰው መሆንን መመኘቱ ከምቀኝነት አይመደብም። ይህ ምኞት ነው የሚባለው። ይህም ወደ መልካም ነገሮች በመሽቀዳደም ላይ ስለሚያግዝ ይፈቀዳል።
- የሰው ልጅ በተፈጥሮው በጥሩ ጉዳዮች ላይ በአንድም ሰው መበለጡን ይጠላል። የሌላው ፀጋ መወገዱ ካስደሰተው ይህ የተወገዘው ምቀኝነት ይሆናል። የሚያስደስተው መብለጥ መቻሉ ብቻ ከሆነ ግን ይህ የሚፈቀደው ምኞት ነው።
- ለገዢ በግዢው ከባድ ሽወዳ እንደተሸወደ መግለፅ በሙስሊም ወንድሙ ገበያ ላይ ጣልቃ መግባት ውስጥ አይመደብም። ይልቁንም ይህ መመካከር ከሚያስፈርደው መካከል ነው። ነገር ግን ይህን የሚነግረው ገዢ ወንድሙን በመምከር ኒያ እንጂ ሻጩን በመጉዳት ኒያ አለመሆኑ መስፈርት ነው። ምክንያቱም ስራ የሚለካው በኒያ ነውና።
- ሁለቱ ተገበያዮች ሳይስማሙና ገንዘብ ሳይለዋወጡ ቀርተው መገበያየት አንድ ሙስሊም በሙስሊም ወንድሙ ገበያ ላይ ጣልቃ መግባት ውስጥ አይመደብም።
- ለአላህ ብሎ መጥላት በሐዲሡ ውስጥ የተጠቀሰው የተከለከለው መጠላላት ውስጥ አይመደብም። ይልቁንም ይህ ግዴታና ጠንካራው የኢማን ገመድ ነው።