/ ነገር አዋሳጅ ጀነት አይገባም።

ነገር አዋሳጅ ጀነት አይገባም።

ከሑዘይፋ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: ነቢዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ: "ነገር አዋሳጅ ጀነት አይገባም።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሰዎች መካከል መቃቃርን ለመፍጠር በማሰብ ወሬን የሚያዋስድ ለቅጣትና ጀነት ላለመግባት የተገባ መሆኑን ተናገሩ።

Hadeeth benefits

  1. ወሬ ማዋሰድ ከትላልቅ ወንጀሎች መሆኑን ፤
  2. ወሬ ማዋሰድ በግለሰቦችም ሆነ በማህበረሰብ ደረጃ ጉዳትና ብልሽትን ስለሚያስከትል ወሬ ማዋሰድ መከልከሉን እንረዳለን።